ፀጋ፥ብርሃን

spiritual-light

                 ፀጋብር

ሲያይዋት ትንሽ ናት።ጠጋ ብለው ሲተነትንዋት ይህ ነው የማይባል ትልቅ ነገር ነች።

ሳይታሰብ ብቅ ትላለች።ቆይታም ሳትወድ ትጠፋለች። ወዳጆቹዋ በነፍስ ግቢና በነፍስ ውጪ ሰዓት ብዙ ናቸው።የልባቸውን ያደርሱ ቀን ግን ተራ በተራ እነሱ እሱዋን እነደማያውቁዋት ጨርሶ ይከዱዋታል።

ከመሣፍንቶች ጋር አንድ ጊዜ አብራ ትቆማለች። „አብዮተኞችም“በጣም አድርገው ያስጠጉአታል።አክራሪዎቹም ያቅፉአታል። ፋሽሽቶቹም እነደ ኮሚኒስቶቹ አላማቸውና ፕሮግራሞቻቸው ላይ ከፍ አድረገው ያስቀምጡአታል።

ሥልጣን ላይ ሲወጡ ደግሞ ብዙዎቹ መልሰው እንደ የሚፋአጅ የፍም እሳት፣ እርግፍ አድረገው ሁሉም ይጥሉአታል። በእግራቸው ቢረግጥዋት -ይረግጡዋትል- ደስተኛ ናቸው።

ለወረጠላት መቼም እንደ ሱዋ „አመቺ“ ነገር የለም። በእሱዋ ስም ይዘምታል። በእሱዋም ስም ገንዘብ ይሰበሰባል። ሰውን ወደ ጦር ሜዳ መሰብሰብ ይቀላል።

ወጣቶች ልጆችም ዕውንት መስሎአቸው ሕይወታቸውን እሰከ መሰዋት ድረስ ይሄዳሉ። ተንኮልኛ አታላዩም፣ ይህን ሰለሚያውቅ እሱዋን ያስቀድማል። 

የዋሁም „ዕውነት“ ነው ብሎ ይህን የሚሉ ሰዎችን ሳይጠይቅና ሳይመራመር ዓይኑን ጨፍኖ ይከተላቸዋል። ሳያውቅ የገባበትን ጣጣና መንጣጣ አደገኛ መሆኑን የሚረዳው ግን ነገር ከእጁ ከአመለጠች በሁዋላ ላይ ነው።… ሲደርስበት ደግሞ ብዙ ነገር አልፎአል።

ልቡን አንዴ የጣቸው ደግሞ፣ ቢያታልሉትም „አሜን“ ብሎ ተቀብሎ ምንተ- ዕፍረቱን ሸፋፍኖ ውስጥ ውስጡን እየተቃጠለ፣ አንገቱን ደፍቶ ይከተላቸዋል።

የተቀረው ዓይኑን እሰከሚከፍት ድረስ በጭፍን መንገዱ አለጥያቄ አብሮ ይጓዛል። የደረሰበት ቀን ግን ወደ ሁዋላ ማለትም እሱንም ይከብደዋል።

ይህን ቀስቃሾቹ በደንብ ያውቃሉ።ይህን ተንኮለኛ አደራጆቹ በደንብ ይጠቀሙበታል።

ማናት ይህቺ፣ አንዳንዴ በሦስት አንዳንዴ በአራት ፊደል የምትጻፈው፣ ነገር ?

ከመሣፍንቱ እስከ ተራ አወናባጁ?… ከፋሽሽቱ እሰከ ኮሚኒስቱ ፣ ከአናርኪስቱ እሰከ ሽፍታው፣…ከቅኝ ገዢው እስከ…ባሪያ ነጋዴው ድረስ የሚያነሱዋት ቃል? 

ሊበርቲ ናት?… ወይስ አርነት?… ነጻነት ናት ወይስ ነጻ- ሰው?…ጥበብ? …ብርሃንና ዕውቀት? ወይስ ጨለማ?…

ሞሰሊን ኢትዮጵያን ሲወር ያስቀደመው ቃል ቢኖር „…የሥልጣኔ ሚሺን፣… ኢትዮጵያን ከባርንት ለማውጣት የታቀደ ዘመቻ… ሲቭላይዚንግ ሚሽን..“ የሚለውን ቃል:- ለማስታወስ ወርውሮ ነበር። የወረራ ዘመቻውንም ያ ፋሽሽት የሰየመውም በዚሁ ግሩም ቃልና ጥሪው ነበር።

ሌኒንና ስታሊን፣ ማኦና ካስትሮ፣ ከእነሱ በሁዋላ የተነሱት ሥፍር ቁጥር የሌላቸው „ነጻ-አውጪዎች፣ እስከ መገንጠል የሚለውን ትግላቸውን“ የቀየሱት፣ ያራመዱት፣ የልባቸውን ያደረሱት፣ በዚህች „አርነት“ በምትባለው ቃል ነበር።

በሌላ በኩል በአፍሪካና በደቡብ አሜሪካ በሕዝቡም ላይ ተነስተው የጨፈሩት ወታደሮች ያራገቡት „ሥርዓትና ቃል…“ ሌላ ሳይሆን ይኸው፣„…አርንትን፣ ..ነጻነትን፣ እኩልነትን፣ ሰበአዊ መብት፣ …ዲሞክራሲን “ነበር። የወታደሩ መንግሥትደርግም ብሎታል።„እናመጣላችሁዋለን…“ በሚለው ውሸት ዙሪያ እስከ አሁን ድረስ ብዙዎች ቆመዋል።

የ20ኛው ክፍለ ዘመን የውሸት ፖለቲካም በብዙ አካባቢ የተመሰረተው ፣በዚሁ አታላይ ቃል ላይ ነው። እላይ ከተጠቀሱት ቡድኖችም ውስጥ አንዳቸውም የገቡበትን ቃላቸውን እስከ አሁን ድረስ አላከበሩም።

እንግዲህ ነገሩ ያላው እነሱ ጋ ሳይሆን እኛው ጋ ነው። prosaune1

„ነጻነትን፣…በሌላው አካባቢ እንደሚባለው፣ ሊበርን፣…ጥብብን፣ ብርሃንና ዕውቀትን…“ እባካችሁ ስጡን፣ እባካችሁን አምጡልን ብለን፣ ማንንም የምንጠይቀው ነገር ሳይሆን ፣ እኛው ነጥቀን የምንወስደው ነገር ነው።

መሬት ላይ የወደቀውን ነገር ብድግ አድርጎ የእራሳችን ማድረጉ ደግሞ ወንጀል አይደለም። ለዚህ ደግሞ ዕውነቱን ለመናገር፣ „ግብ ግብም፣ጦርነትም” የሚባለው ነገር ውስጥ መሄድ አያስፈልግም ።

ማመዛዘናና ነገሮችመመልከት፣… ማሰብና ያሰቡትን ነገር መናገር፣… መጻፍና መወያየት፣ መከራከርና መተቸት፣ እኛ የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ወይም አቴኢስቶች እንደሚሉት „ከተፈጥሮ“ ያገኘነው ፀጋና ስጦታ ነው። ለምን አምባገነኖች ይህቺን መብት ይፈሩአታል?

አንድ አምባገነን ሥልጣኑን መከታ አድርጎ ብዙ ነገሮችን „አታድረጉ ብሎ አንድን ሕዝብ ሊከለክል“ ይችላል። ማሰብን ግን እሱ ጨርሶ መከልከል ይችላል? በምንም ዓይነት፣ ማሰብን መከልከል አይችልም። በምን አቅሙ ነው፣ የአንድ ሰው ጭንቅላት ውስጥ ገብቶ ሊከለክል የሚችለው? ይህማ አስቸጋሪ ነው።

ምሮ ያሰበውን፣ የታሰበውንስ ቀና ሐሳብ ከሌላው ጋር ለመነጋገር (ምንም ዓይነት ሥልጣን ቢኖረው) ማንም ሰው ማንንም ሊያግደው አይችልም ።

እንግዲህ አሁን ያለነው፣ በዚህ „ፀጋ-ብርሃን“/ዘመነ፥ብርሃን በሚለው ጽሑፋችን እሱን አንስቶ መመልከቱ ላይ ነው። አምባገነኖች የእያንዳንዱን ግለሰብ ነጻነት፣ ለምን እንደጦር እንደሚፈሩ በየጊዜው አንስተን እንመለከተዋለን። 

እንግዲህ ይህ አንደኛው  አርዕስት ነው።

ሁለተኛው ስለ ጋርዲያን ጋዜጣ ነው።የምዕራቡ ዓለም ስለ ሚኮራበት ስለ ፕሬስ ነጻነት፣ ስለዚያም አታሚዎች ፍተሻ ፣ስለ ጋርዲያን ጋዜጣ ነው። ቻይና በዚህ ጉዳይ ላይ ምን እንዳለች አስተያየቱዋን ፈልገን ለማውጣት አስበን ነበር። አልተሳካልንም። ግን አገላብጣችሁ እንደምታዩት የሌሎቹም አስተያየት ቀላል አይደለም።

ሦስተኛው  አርዕስት„ ….እኛ ጥቁሮች እራሳችንን በእራሳችን፣ ተመካክረንና ተቻችለን ተፈራርቀን መግዛት ስለ አልቻልን፣ የዱሮ ጌቶቻችን ነጮች መጥተው ይግዙን…“ በሚለው አዲስ ጥሪ ላይ ያተኩራል።

ይህ ደግሞ ምን እንበላው „…ያሳዝናልም። ያስቃልም። ያቃጥላልም። ይኮረኩራልም። ….“ ወቸ ጉድም ያሰኛልም። በተጨማሪም አወዛጋቢ ሰለሆነው የግብፅ ጉዳይ ያለንን አስተያየትና፣ እንዲሁም ስለ ውርሰ፥ቅርስ ለመነሻ ያህል የደረሰንን ሰነደንና  የሰዓሊው የእስክንድር ቦጎስያን ማስታወሻችንንም ተመልከቱት።

ዋና አዘጋጁ

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

 

——————

About ለ አእምሮ / Le'Aimero

አሳታሚው፥ ይልማ ኃይለ ሚካኤል - Publisher:- Yilma Haile Michael, Journalist
This entry was posted in ርዕስ አነቀጽ / Editorial. Bookmark the permalink.

Leave a comment