የአድዋ ድል 118ኛ ዓመት

የአድዋ ድል 118 ዓመት

Battle of Adwa

የአድዋ ጦርነት

ዛሬ በየካቲት 23፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቀን 1888 ዓ.ም.  ከጠዋቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በአሥራ አንድ ሰዓት ላይ የአድዋ ጦርነት ሲጀመር 118 ዓመት ይሆነዋል።*1

የአድዋን ድል 118ኛ ዓመት ለማስታወስ ስለ ዳግማዊ  ምኒልክ ና የአድዋ ገድል :-

_

ጀግንነትና   የአዋቂ ሰው ሥራ ታሪክ

የዘመናዊ ፖለቲካ አሠራር አጀማማር በኢትዮጵያ

*

ዳግማዊ ምኒልክ / Emperor Menelik II of Ethiopia

ዜናው ተናፍሶ ወሬው ዓለምን አዳርሶ ጥቁሩንም ነጩንም ቀዩንም ፍጡር ከዚያም ራቅ ብለው  የሚኖሩትንም ቢጫውንም  ሕዝብ ያኔ ከነበሩት ከእነጌቶቻቸው ያስደነገጠው  አንድ ነገር ቢኖር አደዋ ነው። *2

ትንሽ ቆይቶም ዜናው በቅኝ ግዛት መዳፍ ሥር ነጻነታቸውን ተገፈው የሚኖሩትን ያኔ „ባሪያዎች“ ተብለው የተናቁትን ሕዝቦች  የልብ ልብ ሰጥቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ያስደሰተው  በሁዋላም እንደምናነበው የታሪክ ጸሓፊዎችንም በብዙ ቦታ በጣም ያስገረመው  የአደዋ ጦርነት፣ የተጀመረው በየካቲት 23 የቅዱስ ጊዮርጊስ ቀን 1888 ዓ.ም.  ከጠዋቱ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በአሥራ አንድ ሰዓት ላይ ነው። በዚህ በትክክል በስንት ሰዓት በሚለው ጥያቄ ላይ የተለያዩ ግምቶችና ማስረጃዎች -ከተለያዩ ሰዎች ይቀርባሉ። 

በአንድ በኩል    …ጦርና ጋሻ አንካሴና ጎራዴ፣ውጅግራ ጠበንጃና ምንሽር የያዙ ብሎኮና ነጠላ በርኖስና ካባ የደረቡ በባዶ እግራቸው የሚሄዱ ሰዎች ተሰልፈዋል።  በሌላ በኩል …ይህን ያህል ሺህ ወታደሮች መድፍና መትረየስ ቦንብና ዘመናዊ ጠበንጃ ሽጉጥና ሴንጢ ይዘው ታጥቀው በጥይት ሊቆሉአቸው መለዮ ኮፊያቸውን አድርገው ተደርድረው መሽገው ቆመዋል ።

የቀረውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ….(እንደገና የታተመ)

*1 – እአአ ማርች 1 ቀን 1896 (1st of March 1896) ተዘግቦ እናገኛለን!

*2 When Ethiopia Stunned the World

Book Review: The Battle of Adwa: African Victory in the Age of Empire

(April Review, 2012)

_

አእምሮ የካቲት 2006 / February 2014/ እትም፣ቅጽቁጥር-7

About ለ አእምሮ / Le'Aimero

አሳታሚው፥ ይልማ ኃይለ ሚካኤል - Publisher:- Yilma Haile Michael, Journalist
This entry was posted in ሌሎች / others. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s