የሐምሌ 2005 / July 2013 እትም፣ ቅጽ 1፣ ቁጥር 5

leaimero-July-01-b

cropped-leaimero-new8b-head3.jpg

ለ አእምሮ ፥ ቁ– I-05/7-5

የሐምሌ 2005 / July 2013 እትም…ቅጽ 1 ፣ቁጥር 5

_____________________________________

zeichen-amha-full

ሀሌታው “ሀ” ከሁሉም በፊት የነበረ በግሪክ ወይም በላቲን “አልፋ”የሚባለው ቃል ነው።

የግዕዙ”ሀ” አገርም “ሀገርም” ማለት ነው።

leaimero-Amharic-le

ለ — ለአ እምሮ ነው ።

የባህላችን ዕድገት ፣ የምንኮራበትና ልናጌጥበት የምንችለው፣ አንዱ ነገር ቢኖር (እሱ ብቻ አይደለም) በፊደላችን ነው። ጥቂት አገሮች ናቸው የራሳቸው ፊደል ያላቸው። አንደኛው ደግሞ እኛ ነን።

ይህ የፊደል መጀመሪያው – “ሀ” – ፣ እንዲሁም የሰው ልጅ ታሪክ ያዘለው ፊደላችን፣ እንኳን ለኛ፣ ለዓለምም እንደ ሰው ልጅ “ባህላዊ ቅርስ ተጠብቆ” የሚቆይ ነው።

በነዚህ በምንኮራባቸውና ከማንም ህዝብ ያላነሰ ልንታይባቸውና ልንገለገልባቸው በምንችለው ፊደሎቻቻን፣ ብዙዎቹ ያልቻሉትን፣ እኛ ግን ማንም እንደሚያውቀው ፣ መጽሐፍ ቅዱሱን ፣ ቅዱስ ቁራኑን፣ መጽሐፈ ቁልቁልን ፣ ሰምና ውርቁን፣ ቅኔውን፣ ድርሰቱን ፣ዜማውንና ቅዳሴውን ፣ ታሪካችን ሳይቀር ተጽፎበት ዛሬ እናነበዋለን። በመቶና ከዚያም በሚበልጡ ፊደሎች ደግሞ ጋዜጣ አትሞ ማውጣትም ይቻላል።

በጥቂት ፊደላትም ብዙ ነገር መናገር ይቻላል። “ሰምና ወርቁ” ልዩ ምስክር ነው። ወስጠ ወይራና አሽሙር፣ ሽሙጥና ቅኔ፣ ግሩም ነገሮች ናቸው። አዝማሪው ይችልበታል። ገጣሚው በቃላት መጫወትን ያውቅበታል። ጋዜጠኛው፣ ጸሐፊው፣ ተቺው፣ ዕድሉን ቢያገኙት እንደ ሌሎቹ ፣ፊደሉን ያሽከረክሩታል።…

ከአንድ መቶ በላይ የሆኑ ፊደላት ሲገጣጠሙ ደግሞ ፣ እላይ እንደተባለው መጽሐፍ ቅዱስን ፣ ከዚያም አልፎ (ደካማ ምላሶች እንደሚሉት ሳይሆን) ቅዱስ ቁራንን፣ መጽሐፈ ቁልቁሉን፣ በግዕዝ ፊደል ተርጉሞ መጻፍም ይቻላል። እንግዲህ ብዙ ፣የሚቀራረቡና የማይራራቁትን ቋዋንቋዎችንም ማስተናገድ (በትውልዱ መካከል መስማማት ቢኖር) ጨርሶም ባልከበደው ነበር 1)። ከመቶ በላይ በሆኑ ፊደላት እንደ “ፍቅር እሰከ መቃብርን ” የመሰለ ልብ ወለድ ድርሰት ተደርሶአል። ” የኢትዮጵያ ታሪክን”፣ “የሔሮዶቲስን” ጥንታዊ ጽሑፍ ፣ የቮልቭጋንግ ጉተን ሥራዎች ተርጉሞ ማቅረብም ተችሎአል።

ግን ፊደላትና ቃላትን ዝም ብሎ መገጣጠም ብቻ ሳይሆን ( ያ! እንዳየነው ወደ ጥራዝ ነጠቅነት ይወስዳል) አንድን ነገር ጽፎ ለንባብ ማቅረብ ፣ በመጀመሪያ ማሰብንና ማሰላሰልን ፣ረጋ ብሎ ማጥናትን ፣ ከሒሊና ጋር መሟገትን፣ ፕላን ማውጣትን ፣ መሰረዝ መደለዝን ፣ መጠንቀቅን ፣እረስንቱን….ይጠይቃል።

ፊደል :-የእራሱ ፊደል ያለው ሕዝብ፣ መዓት ዕለታዊ፣ ነጻ-ጋዜጣዎችንም ከነ መጽሄቱ፣ አሳትሞ ማውጣት ይችላል። ይህ ግን አልተቻለም። ለምን?

የዛሬውም ጽሑፋችንም በዚሁ” በፕሬስ ” ጉዳይ ላይ ያተኩራል።

ለምንድነው በምዕራቡ ዓለም “በካፒታሊዚም ሥርዓት” ነጻ -ጋዜጣ ፣ ማለት የፕሬስ ነጻነት የተስፋፋው፣ የተፈቀደው?…የተከበረው? ለምንድነው በተቃራኒው ይህ የጋዜጠኞች መብት፣ በምሥራቁ ዓለም ፣ በኮሙኒዝም፣የአገዛዝ ዘመን የተከለከለው? እንደ ወንጄልም ተቆጥሮ ጋዜጠኛን የሚያስከስሰው? ለምንድነው ኮሙኒዝምና ስታሊንዚም እንደዚሁ ፋሺዚም፣ ነጻ ፕሬስን ፣ ነጻ-አስተሳሰብን ሁለቱ ሥርዓቶች ተመካክረው ይመስል ፣ ፈጽሞ የማይወዱት? አሳደውም፣ ሁለቱም የሚያጠፉት?

ለምንድነው በምዕራቡ ዓለም ሰው በነጻ- መደራጀት የሚችለው? የፈለገውንም ድርጅት መምረጥ፣ለእሱ የተፈቀደለት?

ለምንድነው የምርምር ነጻነት ፣ የመጠየቅ መብት መቃወምና መተቸት እዚህ ፣ አውሮፓ እዚያ አሜሪካ የተፈቀደው? በተቃራኒው፣ ቻይናና ሰሜን ኮሪያ፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ የተከለከለው?

እንግዲህ እነዚህን ሁሉ ጥያቄዎች ቀስ እያለን ተራ በተራ መለስ ብለን እንመለከታቸዋለን።እንዳልነው ዛሬ በፕሬስ ነጻነት እንጀምራለን።

መልካም ንባብ፣ መልካም ቆይታ!

አዘጋጁ ይልማ ኃይለ ሚካኤል።

___________________________________

zeichen-amh-july

ስለ ትችት እነደ መብት፣ ትችት እንደ ሙያ፤ ስለ ጋዜጣና ጋዜጠኛነት፣የፕሬስ ነጻነት

https://i1.wp.com/www.unmsp.org/wp-content/uploads/2011/12/journalist.png

***

“የሰው ልጆች በሙሉ ፣ በትውልድ

ነጻ እና አኩል መብት በሕግ ፊት አላቸው።” 1789 የፈረንሣይ ሽንጎ አዋጅ።

zeichen-amha-full

እንዴት ደሰ ይላል ቅዳሜና እሁድ ወይም ከሥራ መልሰ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሎ ከቤተሰብ ጋር እየተወያዩ የዕለቱን (የተለያዩ) ጋዜጣዎች ሲያገላብጡ።

እጅግ ደስ ይላል ቡና ቤት ቁጭ ብሎ ጋዜጣዎችን፣ ከቢራ፣ ወይም ከሻይ፣ ወይም ከአፕሬቲፍ ጋር፣የተለያዩ ሐሳቦችን ሲያጣጥሙ። በጣም ደስ ይላል አውሮፓና አሜሪካ መጽሔትና ጋዜጣ እቤት ድረስ በፖስታ መጥቶ የቁርስ ጠረጴዛ ላይ ሲዘረገፍ። የለመዱት ጽሑፍም ተከትሎ ያደሩበት ሆቴል ከተፍ ሲል እንዴት ደስ ይላል።

ግን ደግሞ እንደምናቀወቀው፣ይህን የመሰለ ሁኔታ ሁሉም ቦታ አይታይም። አንዱ “ጉልበተኛ አምባገነን” መጥቶ፣ ሁሉንም ጋዜጠኞችን እሥር ቤት ወርውሮ ቢሮአቸውን ዘግቶ „…ከዛሬ ጀምሮ የቡርጃ የአደሃሪዎች ቅጠሎች ፣ እንዳይታተሙ በአዋጅ ተከልክሎአል” ሊልም ይችላል። በእጁም የተገኘውን አብሮ ሊቀጣውም ይህ ፍርደ ገምድል ይችላል ።

ብዙ ቦታ እንደዚህ ተደርጎአል። ብዙ ቦታም የጋዜጠኞች ሥራ እንደ ወንጄል ተቆጥሮ ታስረዋል። ተገድለዋል። ያመለጡትም ተሰደዋል።

የቀረውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ…

ስለ ትችት እነደ መብት፣ ትችት እንደ ሙያ፤ ስለ ጋዜጣና ጋዜጠኛነት፣የፕሬስ ነጻነት

________________________

1) http://leaimero.com/2013/07/03/origins-and-usage-of-geez/

About ለ አእምሮ / Le'Aimero

አሳታሚው፥ ይልማ ኃይለ ሚካኤል - Publisher:- Yilma Haile Michael, Journalist
This entry was posted in ለ አእምሮ አዲስ እትም, ርዕስ አነቀጽ / Editorial. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s