በሥልጣን መባለግ! ለምሳሌ በቱርክ አገር

በሥልጣን መባለግ! ለምሳሌ በቱርክ አገር

ጠግበው ማለት እንችላለን ፣ የሚቆጣቸው ሰው ምን ያድርጉ ጠፍቶ፣ የቱርክ ሸንጎ አባሎች፣ ከዚያ የደረሰን ዜና እንደሚለው፣ „ ዕድሜ ልክ ድረስ የሚቆይ መብትና ጥቅም ለእነሱ ብቻ ለማስከበር“ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት አባሎች፣ በጋራ ተነስተዋል።

በቀይ መብራት ላይ መኪናቸው፣ እንደማንኛውም ተራ ሰው፣ሕጉን አክብሮ እንዳይቆም፣ አነሱ፣ አንካራ ላይ ጠይቀዋል። ግን እንዴት አድርገው?

ቀይ የዲፕሎማቲክ መታወቂያ ወረቀት (ፓስፖርት) ያላቸው፣ የሸንጎ አባሎች፣ “ሱድ ፣ ዶቸ ሳይቱንግ „ የተባለው የጀርመኑ ዕለታዊ ጋዜጣ እዚህ እነደጻፈው፣ እነሱ „እያውለበለቡ ከቀረቡ፣ በቀይ መብራት ላይ ሌሎቹ፣ ሲያቆሙ የእነሱ መኪና ትራፊኩን አቋርጦ፣ መሄድ፣ እንዲፈቀድላቸው „ ጠይቀዋል።

ሌላስ የሚመኙት ነገር አለ?

ሽጉጥ፣ ጠበንጃ፣ እና ከባድ መሣሪያ ለመያዝ ከፈለጉ ደግሞ፣ የቱርክ አገር ጋዜጣዎች እንደጻፉት፣ „ዕድሜ ልካቸው ድረስ ይህን እንደፈለጉት፣ እንዲሰበስቡና እንዲያከማቹ የሚፈቅድላቸው፣ አንድ ልዩ ፈቃድ፣ ለሁሉም የሸንጎ አባሎች“ ቀጥለው፣ ጠይቀዋል።“

ይህንን እና ሌሎች ምኞታቸውን የሚያረካላቸውን የሕግ አርቃቂ ቡድን ከመካከላቸው ከመረጡ ወዲህና ፣ ተራው ሕዝብ ጆሮ ውስጥ ነገሩ ከገባ ጊዜ ጀምሮ ደግሞ፣ አሁንስ አበዙት የሚሉ ሰዎች ቁጥር፣ በቱርክ እየተበራከተ መጥቶአል። እንዲያውም፣ መሳቂያ ና መቀለጃ፣ አሻንጉሊቶች፣ ጋዜጣዎች እንደአሉት፣ እነሱ በገዛ እጃቸው፣ አሁን ሁነዋል።

„በሚቀጥለው ሕይወቴ፣ እንደገና ከተወለድኩ“—አንዲት የቤት እመቤት ለሚመለከተው ሰው ሁሉ ብላ በአናፈሰቺው ትዊተር፣ ላይ፣ እሷ— „….አለጥርጥር የሸንጎ ኣባል፣ የሕዝብ እንደራሴ ለመሆን እፈልጋለሁ!… እሆናለሁ!“ ብላም፣ እኛ እዚህ እንዳነበብነው፣ ይህች ሴትዮ ፎክራለች። አኛም መሆን እንፈልጋልን ብለው፣ አንዳዶቹ፣ ድርጅት መፍጥር ጀምረዋል።

የአንድ ጋዜጣ ሐተታ ጸሓፊ፣ ይህማ፣ አሁን ፖለተከኞቹ የሚያነሱት ጥያቄ፣ ዱሮ ጥለነው የሄድነው „የአንድ የጠገበ ሱልጣን ሕግ ነው“ ብሎ ተቆጥቶ፣ ያ ጸሓፊ፣ እዚያው ላይ አከታትሎ ፣ ጀርመኖች ተርጉመው እዚህ ለእኛ እንደአስቀመጡት፣ „ምንአለበት እግረመንገዳችሁን፣ ኃጢአታችሁን ከላያችሁ ላይ አጥባችሁ የምታራግፉበት፣ አንድ የሐማም፣ የሙቀት ጢስ፣ መታጠብያ ቤት፣ በመንግሥት ገንዘብ እንዲሰራላችሁ አብራችሁ ማመልከቻችሁን፣አሰገቡ፣ ብታስገቡም ይጠቅማችሁዋል“ ብሎ፣ ይኸው ፣ጸሐፍ ቀልዶባቸዋል።

የሕዝብ እንደራሴዎቹ የጠየቁት ጥያቄ፣ ለእራሳቸው ብቻ ሳይሆን ምን አለበት ፣ ዘመዶቻቸውን ፣ ቤተሰቦቻቸውንም ቢጨምር፣ መልካም ነው። ያ ቢሆን እንዴት ጥሩ ነበር ብሎ አንዱ፣ ተንኮለኛ ጋዜጠኛ፣ በሌላ ቦታ በአምዱ ላይ እነሱን መክሮአቸዋል።።

እንደ አነበብነው፣ እነሱም አስበውበት „በእርግጥ ለክፉም ለደጉም „ብለው፣ በተለይ በቀዩ የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት፣ ቤተሰቦቻቸው፣ በሙሉ በዚያ መታወቂያ ወረቀት፣ ቀይ፣የትራፊክ መብራቱን ጥሰው እንዲንቀሳቀሱ፣ „የቤተሰብ፣ ልዩ ፈቃድ „ ጠይቀዋል። ብልጦች ስለሆኑም የቱርክ የሸንጎ አባሎች፣ ይኸው „ሱድ ዶቸ ሳይቱንግ“ የተባለው ጋዜጣ፣ ሰሞኑን እዚህ እንደጻፈው፣ ያንን ልዩ ቀይ ፓስፖርት ለዕድሜ ልክ፣ እንደገና ፓርላማም፣ ውስጥ ተመልስው፣ በሕዝቡም ተመርጠው ባይገቡም፣ እንዲሰጣቸው ጥይቀዋል።

መቀለጃ እየሆኑ የመጡትን የሸንጎ አባሎች ጥያቄ፣ አስተካክላለሁ ብለው፣ የፓርላመው ፕሬዚዳንት፣ የሰነዘሩት ቃል፣ የባሰ ነገሩን አተረማምሶ፣ ሌላ ቦታ፣ እነሱን አሁን፣ ከቶአቸዋል።

ሚስተር ቸሚል ቺቼክ፣ የፓርላማው ፕሬዚዳንት፣ „ ይህ አሁን የታሰበው አዲስ ሕግ“ በእሳቸው ዓይን “ … በተለያዩ ቦታዎችና አንቀጾች ሥር፣ ተበታትነው የሚገኙትን ደንቦች ሰብሰብ አድርጎ አንድ ላይ ለማስቀመጥ ነው „ ብለው የተቆጣውን ሰው ለማረጋጋት የወረወሩት አነጋገር፣ ሌሎቹን፣ ተራውን ሰው፣ የባሰ ነገር ውስጥ ከቶአል።

እነሱን ብቻ ሳይሆን በተለይ የተለያዩ የቱርክን ጋዜጣ አዘጋጆችና ጸሓፊዎችን፣ ነገሩ ዕብድ እዚህ እንደጻፈው፣ አድርጎታል። ጎልጉለው አንዳዶቹ፣ በየሦስት ወሩ ፣ ማለት በአመት አራት ጊዜ፣ የአመት ደመወዛቸውን፣ በአንዴ የሚቀበሉትን የሸንጎ አባሎች፣ የሒሳብ አከፋፈል ብዙዎቹ አንስተው፣ ተገቢ አይደለም ብለው፣ በቅጠሎቻቸው ላይ፣ ተችተዋል።

እንደዚህ ከሆነማ „ ጸሓይ ስትወጣ ፣ በጥሩ አየር፣ ምግባቸውን በመሶብ፣ ከብር ስልቻ ጋር፣ ደጃፋቸው ላይ አሰቀምጠን ፖለቲከኞቻችንን „ አንድ ተንኮለኛ ሠዓሊ“፣ እናስደስታቸው „ የሚለውን ሐሳቡን፣ ቱርክ ውስጥ አሰራጭቶአል።

„የቁንጅና ቀዶ-ጥገናም፣ አብሮ“ ነጻ የሕክምና ወጪ በመንግሥት ሒሳብ ፣ የሚሰጣቸው ከሆነ፣ „…አብሮ እንዲሰጣቸው“ አንድ ፣ የተቃዋሚ ጋዜጣ ጠይቆአል።

አንድ የብሔራዊ ፓረቲ አባል ሚስተር ኡቻን ይንቸሪ፣ ሳይቸግራቸው የተናገሩት ቃል ፣ ጀርመኖች እንድጻፉት፣ ቱርኮችን አበሳጭቶአል። „ …ፖለሶች አቁመውን በፍጥነት ትከንፋላችሁ ብለው እኔንና ሹፌሬን፣ መንጃ ፈቃዳችሁን አሳዩን ብለው የስጨነቁንን ነገር እኔ፣ ምንም ጊዜ፣ አልረሣውም። ቀይ ፓስፖርት ቢኖረን ይህ ሁሉ ነገር አይድርስብንም ነበር።“ ሰውዬው ያሉት አሁንም ድረስ ሰውን አስቆጥቶአል።

አሁን በመኪና አደጋ የሚሞቱ ሰዎችን ጉዳይ የሚከታተል አንድ ድርጅት ተጠሪ እንደአሉት፣ „ የሸንጎ አባሎቹ እንደፈለጉት በቀይ መብራት መክነፍ ወደፊት የመያመጣው አደጋ ቀላል አይሆንም ብለው፣ „ ሰውዬው አስጠንቅቀዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚንስተሩን፣ ሽንጎው፣ ውስጥ የተቀመጡ ፣ ተቃዋሚዎቹም ሆኑ ሥልጣኑን ፣ አሁን የጨበጡት ድርጅቶች ተጠሪ፣ ሁሉም በጋራ በአዲሱ ሕግ ላይ መስማማታቸው፣ ነገር ግን ፣ ሕጉ በአስቸኳይ እንዳይተላለፍ ፣ ማዝገማቸው፣ ሰውዬውን፣በጣም አድረጎ አስገርሞአቸዋል።

አሁን ሁሉም ይንጫጫል እንጂ፣ ነገ ዞር ብሎ ሕጉን፣ ቢተላለፍ የሚቃወም የለም የሚሉ አንድንድ ፖለቲከኞች፣ አልጠፉም የሚሉም ሰዎች እዚህ አሉ። ባጠቃላይ ሲታይ ግን ብዙዎቹ የሕዝብ እንደራሴዎቹ፣ ኃይለኛ ስጋት ውስጥ –ጀርመኖቹ እንደጻፉት፣ እነሱ አሁን ስጋት ውስጥ ገብተዋል።

አንድ የግራው ክንፍ ድርጅት ተጠሪ፣“…እኔ ስለ አዲሱ ሕግ፣ ይዘትና መልዕክት ምን እንደሆነ ምንም የማውቀው ነገር የለም።… እኔ አብዛኛውን ጊዜ ከፓርላማው ውጭ፣ ከሕዝቡ ጋር በገጠር ጊዜዬን አጠፋለሁ“ ያለውን አነጋገር፣ ዘጋቢው፣ ለእኛ እንደጻፈው እሱንም ቢሆን የሚያምነው፣ ሰው የለም።

„የእኛን መብት እንደፈለጉት፣ ፖለቲከኞቹ እንደፈለጉት፣ ይሽሩታል ፣ ይቀይሩታል። ለእራሳቸው ሲሆን ግን፣ ለእነሱ እነደሚያመች አድርገው፣ እንደ ግልቤታቸው የሕዝብና የመንግሥት ሀብትን እንደፈለጉት“፣ አንድ የሠራተኛው ማህበር ተጠሪ እንዳለው፣ ሕግ አውጥተው፣ „ይዘርፉታል።“

አንዱ ቀልደኛ እኔ ጥሩ መፍትሔ አለኝ ብሎ፣ ብቅ ብሎአል። በእሱ እምነት መድሓኒቱ፣ ቱርክ ለገባችበት ችግር መፍትሔው፣ አንድ ነገር ብቻ ነው። „የሕዝብ እንደራሴዎቹ ቁጥር በሸንጎ ውስጥ ከፍ ይበል“ ይላል። „አሁን ፓርላማ ውስጥ ከአሉት 550 አባሎች ፋንታ፣ ቁጥራቸው፣ ትንሽ ስለሆነ፣ ከፍ ብሎ፣ 75 ሚሊዮን እንዲሆኑም „ ይጠይቃል። „ችግራችን ያኔ ይፈታል“ ብሎም ግምቱን ሰንዝሮአል።

———————

leaimero-reg-logo © ለ አእምሮ 2005 / © Le’Aimero Copyright 2013

About ለ አእምሮ / Le'Aimero

አሳታሚው፥ ይልማ ኃይለ ሚካኤል - Publisher:- Yilma Haile Michael, Journalist
This entry was posted in ሌሎች / others. Bookmark the permalink.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s